ልጥፎች

“በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻ አወጣን።”

ምስል
ገላትያ 5፡1፤ ያዕቆብ 5፡ 14 ፤ ሐዋ 3፡ 1፤ መዝ 40፡ 3 ፤ ዮሐ. 5፡ 1  የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት ላይ ነን። መጻጕዕ ይባላል። ይኽ ሳምንት ጌታ ኢየሱስ ድውያንን መፈወሱን የምታስብበት ነው። በጾመ ድጓዋ “ብውሕ ሊተ እኅድግ ኃጢኣተ በዲበ ምድር፤ እስብክ ግዕዛነ፣ ወእክሥት አዕይንተ ዕውራን፤ አቡየ ፈነወኒ።” (በምድር ላይ ኃጢኣትን ይቅር እል ዘንድ፣ ነጻነትን እሰብክ ዘንድ፣ የዕውራኑን ዓይኖች እከፍት ዘንድ አባቴ ላከኝ) እያለች ወልድ ከአብ ዘንድ ተልኮ ነጻ ያወጣን ዘንድ እንደመጣ ትዘምራለች። በወንጌል የተጠቀሱትን የጌታ የፈወሳቸውን እየጠቃቀሰች ታዜማለች። ከደስታዋም ብዛት “በሰንበት ፈወሰ ዱያነ፤ ወከሠተ አዕይንተ ዕውራን በሰንብተ፤ ፈድፋደ ኪያነ አፍቀረነ።” (በሰንበት ሕሙማንን ፈወሰ፤ የዕውራኑን ዓይኖች ከፈተ፤ እኛን እጅግ ወደደን!) ትላለች። በዚኽ እሑድ የሚነበቡት ምንባባትም ኹሉ ስለ ሕመም፣ ስለ ፈውስ እና ስለ ነጻነት ይናገራሉ። ዋናው ጉዳይ ግን መታመም ወይም መፈወስ ሳይኾን እግዚአብሔር በአንድ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በሠራውና ዛሬም አካሉ በኾነችውና መንፈሱን በለበሰችው ቤተክርስቲያኑ በሚሠራው ሥራ ለሰው ልጅ የሰጠው ዘለዓለማዊ ግዕዛን (ነጻነት) ነው። በዚኽ አጀንዳ ላይ ሰዎች የእግዚአብሔርን ሐሳብ ምን ያኽል እንደማይረዱት በዮሐንስ ወንጌል 5 ላይ ያለው ለ38 ዓመታት ታምሞ የኖረው ሰው ታሪክ በግልጽ ያሳያል። በዚኽ ታሪክ ውስጥ ሦስት የተለያዩ አካላትን እንመለከታለን።    አንድ፦ ታማሚው ሰው  ታማሚው ሰው 38 ዓመት በሥቃይ ኖሯል። ተንገላትቷል። ፈውስ ጠብቆ አላገኘም። ሮጦ መያዝ፣ ሠርቶ መክበር፣ ሌሎች ሰዎች የሚያደርጉትን ማድረግ አልኾነለትም። ስለዚኽ፣ “ከሰዎች አንሻለኹ! ስላነስኹም እኔን የሚወድደ...

መብዛት፣ መጾም እና መቀደስ

ምስል
  “ከፊት ይልቅ ትበዙ ዘንድ በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን።” ኤፌ 4፡ 11 “ περισσεύητε” ፩ ተሰ ም. ፬፥ ቍ. ፩-፲፫ ፤ ፩ ጴጥ፡ ም. ፩፥ ቍ. ፲፫-ፍ፡ም ፤ ግብ፡ ሐዋ፡ ም. ፲፥ ቍ. ፲፯-፴ ፤ መዝሙር፡ ፺፭(፺፮)፥ ቍ. ፭-፮። ማቴዎስ፡ ም. ፮፥ ቍ. ፲፯-፳፭ የዐቢይ ጾም ኹለተኛ ሳምንት ላይ ነን። ሳምንቱ ቅድስት ይባላል። ከዚኽ ሳምንት ጀምሮ እስከ ሆሳዕና ድረስ ያለው ጊዜ "ጾመ አርብዐ"፣ "ጾመ ኢየሱስ" ይባላል። ለዚኽ እሑድ የተመደቡት ምንባቦች ኹሉም ቅድስና ምን እንደኾነ፣ ለሰው ልጅ ምን ያኽል አስፈላጊ እንደኾነና የቅዱስ ሰው ኑሮም ምን መልክ እንዳለው ይናገራሉ። መዝሙረኛው “ምሥጋናና ውበት ሰማያትን በሠራው በእግዚአብሔር ፊት፣ ቅድስናና ግርማም በመቅደሱ ውስጥ እንደኾኑ” ይዘምራል። ጌታ ኢየሱስም “ስትጾሙ እንደግብዞች አትኹኑ!” እያለ የእግዚአብሔር ሕዝብ ጾም ምን እንደሚመስል ያስተምራል። ቅዱስ ጳውሎስ “የእግዚአብሔር ፈቃድ የእናንተ መቀደስ ነው” ይላል። ቅዱስ ጴጥሮስ “በኑሯችኹ ኹሉ ቅዱሳን ኹኑ” ይላል። የሐዋርያት ሥራ ጸሐፊው ቅዱስ ሉቃስም በምጽዋቱና በጸሎቱ የሚታወቀው መቶ አለቃ ቆርኔሌዎስ ቅድስናው ይጨምር ዘንድ ጴጥሮስን 40 ማይል ገደማ ርቃ ከምትገኘው ከኢዮጴ ልኮ ሲያስመጣ ሰምተናል። ጾመ ድጓውም “ሰንበትየ ቅድስትየ” እያለ ሰንበትን ከማሞካሸት በተጨማሪ “ተፋቀሩ፡ በምልዓ፡ ልብክሙ። አክብሩ፡ ሰንበተ፡ በጽድቅ፡ ዝግቡ፡ ለክሙ፡ መዝገበ፡ ዘበሰማያት፡ ኀበ፡ ኢይበሊ፡ ወኢይማስን” (በፍጹም ልባችኹ ተፋቀሩ። ሰንበትን በጽድቅ አክብሩ። በሰማያትም ብል የማይበላውና የማይጠፋ ሀብትንን ሀብትን አከማቹ) እያለ እነዚኽኑ ምንባቦች ይዘምራል። እነዚኽን ኹሉ ምንባቦች መብዛት፣ መጾም እና መቀደስ በሚሉ ሦ...

“መንገዱ”

ምስል
የዛሬ ምንባቦች፦ ሮሜ 1፡1-12፣ 1ኛ ጴጥ. 1፡ 13-22፣ ሐዋ 19፡ 1-11 መዝ 47፡7 ፣ ሉቃ 2፡ 36-42 መዝሙር፦ ተወልደ ኢየሱስ የአስተንትኗችን መነሻ ሐዋ 19፡9 ላይ የሚገኘው “መንገዱ” የሚል ቃል ነው። ቅዱስ ሉቃስ በሐዋርያት ሥራ ላይ ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን ከተማ በነበረበት ጊዜ ሲያስተምር አንዳንድ ሰዎች “እልኸኞች ኾነው በሕዝብ ፊት መንገዱን” እንደሰደቡ ይነግረናል። የጥንት ክርስቲያኖች “ራሳቸውን የመንገዱ ተከታዮች” ብለው ይጠሩ ነበረ። የኑሮ ዘይቤያቸውንም “መንገዱ” በግሪክ ὁδὸσ ፣ በሱርስት ደግሞ ܐܘܪܚܐ ፣ በዕብራይስጥ הדרך እያሉ ይጠሩት ነበረ። ስለዚኽ መንገድ ሦስት ነጥቦችን እናንሳና ምንባቦቻችን ምን እያሉን እንደኾነ እንመልከት፦   በእምነት የመታዘዝ መንገድ  ይኽ መንገድ ምን ዓይነት መንገድ ነው ብለን ስንጠይቅ መልሱን ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ ላይ “ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ” ሲል ይመልስልናል። የራሱን ማንነት ለሮሜ ክርስቲያኖች ሲያስተዋውቅም “በአሕዛብ ኹሉ መካከል ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን” ይላል።  በሌላ አባባል፣ አሕዛብን ኹሉ አምነው እንዲታዘዙ ማድረግ የቤተክርስቲያን ቋሚ ሥራዋ እንጂ ሌሎች አካላት እስኪ የአካታችነት (inclusivity) ፖሊሲ ስለቀረጹ፣ ወይም እነእገሌ እነ እገሌንም ያካተተ የስብከት መርሐ ግብር አዘጋጂ ስላሏት አይደለም። ክርስቲያኖች የሚኖሩለትም፣ የሚኖሞቱለትም ሌላ ዓላማ የላቸውምና። በእምነት መታዘዝ መጀመሪያ እምነት ይጠይቃል። የሰው ልጅ በተፈጥሮው አማኝ ፍጥረት ነው። ዕውቀቱ ፍጹም ስላልኾነ ሳያምን መንቀሳቀስ አይችልም። ሌላው ቀርቶ በእግዚአብሔር አናምንም የሚሉ ሰዎች እንኳ አለማመናቸውን ባያምኑ ኖሮ የሚያደርጓቸውን ...

ይኽ ምሥጢር ታላቅ ነው! ኤፌ 5፡ 32

ምስል
  “ዐቢይ ውእቱ ዝ ነገር!”/ “ይኽ ምሥጢር ታላቅ ነው!”/ “τὸ μυστήριον τοῦτο μέγα ἐστίν” ኤፌ 5፡ 32  የትኛው? ሦስት ነጥቦችን ላንሣ፦  እግዚአብሔር ፍጥረትን የወደደበት ዘለዓለማዊ ምሥጢር  ከልግስናው፣ ከደግነቱ፣ ከአፍቃሪነቱ ብዛት ህልውና ያልነበረውን ዓለም ካለመኖር ወደመኖር አመጣው፤ ፍጥረትን ኹሉ ወክሎ ሲጠራ አቤት ብሎ ለተወደደበት ፍቅር ምላሽ መስጠት የሚችል የሰውን ልጅም በፍጥረቱ ላይ ጉልላት አድርጎ አኖረ። ይኽን ያደረገበት ምክንያትም የፍጥረት ራስ የኾነው የሰው ልጅ እግዚአብሔር ፍጥረትን ለወደደበት ዘለዓለማዊ ፍቅር የፍቅር ምላሽ በመስጠት ከእርሱ ከእግዚአብሔር ጋር በፍቅር አንድ አንድ ኾኖ እንዲኖር ነው። በዚኽ አንድ በኾነበት ፍቅርም የእግዚአብሔር ብቻ የኾነው ሕያውነት ኹሉ የሰው ልጅ ሀብት ይኾናል። ክብሩን ይለብሳል። ሕይወቱን ይወርሳል። ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ስለኾነ ከዐፈር የተበጀው፣ ህልውና፣ ሕያውነት የሌለው የሰው ልጅ ሕያው፣ ህልው ይባላል። ሕያው ኾኖም ፍጥረትን ኹሉ ሕያው ያደርጋል። ራሱ ሕያው ከኾነ አካሉም ሕያው ነውና። ይኽ ከእግዚአብሔር ለፍጥረት የተለገሰ ፍቅር ፍጹም ስለኾነ ከሰው ልጅ የሚገኘው ምላሽ ምንም ቢኾን አይለወጥም። በዚኽ ዘመነ አስተርእዮ በቤተ ክርስቲያን የምናስበው፣ የምናመልከውም ይኽንን ዓለም ሳይፈጠር በፊት ጀምሮ የተወደድንበትና ዘመኑ በደረሰ ጊዜ በእግዚአብሔር ልጅ ሰው መኾን የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ዘለዓለማዊ ፍቅር ነው። ዓለም ሳይፈጠር ጀምሮ ለእኛ የነበረው እኛ የእርሱ ኾነን፣ እርሱም የእኛ ኾኖ የመኖሩን ዕቅድ ፈጸመው። ብንበድለው ይቅር ብሎ፣ ብንርቀው ቀርቦ የፍቅሩን ዕቅድ ፈጸመው። ዳግም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ነፋስ እንዳይገባ፣ መተጣጣት እ...

የደነደነ ልብ፣ የታወረ ዐይን፣ የተሰቀለ መሢሕ

ምስል
የዛሬ የግጻዌ ምንባቦች፦ ፩፡ ቆሮ፡ ም. ፪፥ ቍ. ፩-ፍ፡ም ፤ ፩፡ ዮሐንስ፡ ም. ፭፥ ቍ. ፩-፮ ፤ ግብ፡ ሐዋ፡ ም. ፭፥ ቍ. ፴፬-ፍ፡ም ፤ መዝሙር ፬፥ ቍ. ፪-፫ ፤ ዮሐንስ፡ ም. ፱፥፩-ፍ፡ም ።  የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ጌታ ኢየሱስ “እኔ የማያዩት እንዲያዩ፣ የሚያዩት እንዲታወሩ እኔ ወደዚኽ ዓለም ለፍርድ መጣኹ” ሲል ያስሰማናል። መዝሙረ ዳዊት “ልባችኹን እስከመቼ ታደነድናላችኹ?” እያለ ይጠይቃል። በሐዋርያት ሥራ ላይ ቅዱስ ሉቃስ ጴጥሮስና ሐዋርያት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደኾነ በማስተማራቸው እንደተገረፉ ይነግረናል። ቅዱስ ጳውሎስም ለቆሮንቶስ ምእመናን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ከተገደለው ከኢየሱስ ክርስቶስ በስተቀር ሌላ አንዳችም ነገር እንዳልሰበከላቸው ሲያስታውሳቸው ሰምተነዋል። የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ መልእክትም “ኢየሱስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደኾነ ከሚያምን በስተቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው?”  ብሎ ይጠይቀናል፤ ያጠይቀንማል። ያሬዳዊው መዝሙርም ጊዜው ዘመነ አስተምህሮ መዝሙሩም እሑዱ “መጻጕዕ” እንደሚባል መዝሙሩም በዮሐንስ ወንጌል የተነበበውን ምንባብ “ይቤሉ እስራኤል ኢሰማዕነ ወኢርኢነ እም አመተፈጥረ ዓለም ዘዕውሩ ተወልደ” (ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ዕውር ኾኖ የተፈጠረውን ሰው ዓይኖች ያበራ ሰው አላየንም አልሰማንም አሉ” እያለ ያዜማል።  በዐቢይነት የምናያቸው ሦስት ነጥቦች ማንሣት እወድዳለኹ፤ የደነደነ ልብ፣ የታወረ ዐይን፣ የተሰቀለ መሢሕ።      የደነደነ ልብ  በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከፍ ያለ ስፍራ ተሰጥቷቸው ከምናገኛቸው ቃላት ውስጥ ልብ አንዱ ነው። የግሪኮሮማን ሥልጣኔና ቃላት ከመግነኑ በፊት በነበረው የሴማውያን ባህል ልብ የሚለው ቃል ማወቅን፣ መረዳትን፣ ማስተዋልን ያመ...

በእርሱ ኾናችኹ ተሞልታችኋል

ምስል
  “በእርሱ ኾናችኹ ተሞልታችኋል” ( ቆላ. ፪፥ ቍ. ፲-፲፮ ፤  ፩ዮሐ፡ ም. ፪፥ ቍ. ፳፭-ፍ ፤ ሐዋ፡  ፳፪፥ ቍ. ፯-፳፪ ፤ ማቴ ፪፥  ቍ. ፳፪-ፍ፡ም) ባለፈው ሳምንት ልደትን፣ ትናንት ደግሞ ግዝረትን አከበርን። ምንባቦቹ ይኽንን ይዘው የነቢያት ትንቢት መፈጸሙን፣ ጌታ በሥጋ መገለጡን፣ ለቤተ ክርስቲያንም ጸጋውን ማደሉን ይነግሩናል። እኛንም ይኽን እንዲያው የተሰጠንን ጸጋ ታላቅነት እንድናስተውለው፣ እንድንኖረው ያሳስባሉ። ሦስት ነጥቦችን እናንሳ፦   የእመቤታችን ዝምታ (የቤተክርስቲያን ሌላኛው ሥርዓተ አምልኮ) የቤተ ክርስቲያን አምልኮ ሲባል ብዙዎቻችን የምናስበው እንደከበሮና ጸናጽል ያሉ የሙዚቃ መሣሪያዎቻችንን ወይም የሰዓታትና የማሕሌትን ያሬዳዊ ዜማን ይኾናል። ስሕተትም አይደለም። ነገር ግን የቤተ ክርስቲያን አምልኮ ድምፃዊ ብቻ አይደለም። ቤተ ክርስቲያን ኖሮዋ ኹሉ አምልኮ ስለኾነ ድምፅ በማታወጣበት ጊዜም አምልኮዋ አይቋረጥም። ይኽ አምልኮም በእመቤታችን ዝምታ ውስጥ የሚከናወን ነው። እንዴት? ወዳነበብነው የማቴዎስ ወንጌል እንኺድ። ጌታ ኢየሱስ “በነቢያት ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ” በማለት ከልደት እስከ ጥምቀት የነበረውን በእመቤታችን የድንግል ማርያም ዝምታ ውስጥ ብቻ እንድናስተውለው የተሰጠንን የጌታችንን የልጅነት፣ የጉርምስና እና የወጣትነት እድሜ ይጠቁመናል። የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ ኾነ፤ በየጥቂቱ አደገ። ከእናቱ ዕቅፍ እስከ ጉልምስና ለቤተሰቦቹ እየታዘዘ አደገ። የቤተ ክርስቲያን ሊቱርጊያ የጌታችንን ሕይወት እየተከተልን ወደ ጥምቀት እንድንኼድ እየጋበዘን ነው፣ በጽሙና፣ በአርምሞ፣ የተሰጠንን እንድናስተውል እየተጋበዝን ነው። ለምን?...

ንስሐ ግቡ

ምስል
  “ኢየሱስ 'መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ።' እያለ ይሰብክ ጀመረ።” ማቴ. 4፡ 17 ንስሐ ግቡ! = μετανοεῖτε! = ዓላማን፣ ሐሳብን፣ አስተያየትን መቀየር ይህ የጌታችን ስብከት ለአይሁድ መሰበኩ የሚገርም ነው። የእግዚአብሔር ምርጥ ሕዝብ፣ ርስቱ ነኝ ብሎ የሚያስብና ለሚመካ ሕዝብ “ንስሐ ግባ!” የሚል ድምፅ አስደንጋጭ ነው። ምን ያኽል ከእግዚአብሔር ርቆ እንደሚኖር ያሳያልና። እስራኤል እንዴት እዚኽ ደረሱ?  አስተሳሰባችኹን ቀይሩ! ኢሳ. 55፡ 9 “ሐሳቤ እንደሐሳባችኹ፣ መንገዴም እንደመንገዳችኹ አይደለም”  ንስሐ የኃጢኣት ሪፖርት አይደለም!  ዓለምን፣ ሕይወትን፣ እውነትን የምናይበትን መንገድ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ማድረግ እንጂ። ለምን?  አስተሳሰባችን ካልተቀየረ ኑዛዜ አይጠቅመንም። እግዚአብሔር የማያውቀው የኑሯችን ክፍል አለን?  (ታዲያ የኑዛዜ ዓላማው ምንድነው? የኑዛዜ ዓላማው ከተሰለፍንበት ውጊያ እየከዳን የምንሸራተትበትን የኑሯችንን ስፍራ መለየት እንድንችል፣ ጉዟችን የውጊያ ነውና በውጊያው ላይ የሚያቆስሉንን የጠላት ፍላጻዎች በጥንቃቄ እንድንለይ፣ ዛሬ ያቆሰለን ነገ እንዳይገድለን እንድንጠነቀቅ፣ በኃጢኣት በመሰነካከላችን በሚመጣው የሰይጣን ክስ የተነሣ በብቸኝነት ተስፋ ቆርጠን እንዳንደርቅ፣ “እግዚአብሔር ይፍታሕ” በሚለው በካህኑ አንደበት ከቤተክርስቲያን የሚወርደውን የእግዚአብሔር ምሕረት እየጠጣን ለምልመን እንድንኖር ነው።) አስተያየታችኹን ቀይሩ! “መሃይምነት የጨለማ ጉዞ ነው!” ይሉ ነበረ፣ መሃይምነት ምን ማለት እንደኾነ ያላወቁ የ1960ዎቹ “ምሁራን”። እንደርሱ ፎክረው ጀምረውም ማኅበረሰባቸውን ፊደል በፊደል አጥለቀለቁት ግን ፊደል ቋንቋ መጻፊያ ጥበብ እንጂ እንጂ ብርሃን አይደለ...