ልጥፎች

ልጥፎችን ከመለያ ጋብቻ ጋር በማሳየት ላይ

“ወደ ሠርግ ገቡ።” (ማቴ 25 ፣ 10)

ምስል
፩ ቆሮ ፯፥ ፳፭-ፍ፡ም ፤ ፪ ዮሐ፡ ም. ፩፥ ቍ. ፩-፮፤ ሐዋ. ፲፮፥ ቍ. ፲፫-፲፰፤ መዝ፡ ፵፬(፵፭)፥  ፱-፲። ማቴ ፳፭፥ ፩-፲፱  የዛሬ ምንባባት ሠርግ፣ ጋብቻ፣ ቤተሰብ የሚሉ ነጥቦች ተደጋግመው ይሰሙባቸዋል። ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ጋብቻና ስለ ትዳር የለሽነት ይመክራል። ቅዱስ ዮሐንስ በፍቅር ኑሮ በሚገለጠው የኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋ መገለጥ የማመን ሐዋርያዊ እምነት ይጠቁማል። ከሐዋርያት ሥራ የተመረጠው ምንባባችንም ለቤተሰቧ ኹሉ ምክንያተ ድኅነት ስለኾነችው ስለልባሚቱ ሴት ስለልድያ ይተርካል። ምስባኩ “የንግሥት ልጆች ለክብርኽ ናቸው። ንግሥቲቱም ወርቅ ለብሳና ተጎናጽፋ በቀኝኽ ትቆማለች።” ብሎ ስለ ቤተሰባዊ የንጉሡ ክብር ቤተሰባዊ መልክ ምን እንደሚመስል ያሳየናል። ቅዱስ ማቴዎስም ጌታችን ኢየሱስ መንግሥተ ሰማያትን በሠርግ መስሎ ሲያሰተምር አሰምቶናል። ሠርግ፣ ትዳር፣ ቤተሰብ። ይኽ ከእመቤታችን በዓለ ዕረፍት ወፍልሰት ጋር ምን ያገናኘዋል? እስኪ ወደ፣ ሠርግ እና ገቡ የሚሉትን ሦስት ቃሎች ከጌታችን ምሳሌ እንውሰድና ጉዳዩንም ራሳችንንም እንመልከተው።  ወደ  “ወደ” የሚለው ቃል እንቅስቃሴን ያመለክታል። “ወደ” የሚል ቃል ስንሰማ መድረሻውን እንጠብቃለን። ምናልባትም የሰውን ልጅ አጠቃላይ ምድራዊ ኑሮ ያመለክታል። የሰው ምድራዊ ኑሮ በአንድ ቃል ይጠቅለል ከተባለ “ወደ” ሳትገልጸው አትቀርም። ሲፈጠርም ወደ ተደርጎ ነው።  የሰው ልጅ ተጓዥ ነው። ዋሻ ውስጥ እንኳ ዘግቶ ቢቀመጥ ከመጓዝ አያመልጥም። እርሱ ቢቆም እንኳ ጊዜ ተሸክሞት ይኼዳል። ወደደም ጠላም በዚኽ ምድር ላይ ሰው በማያቋርጥ ጉዞ ላይ ነው። እስከ መጨረሻዋ እስትንፋሱ ድረስ እየኾነ ይኼዳል እንጂ ኾኖ አይቆምም። እየኾነ ነው። እየተጓዘ ነው። በአእምሮው ውስጥ የሚ...

ይኽ ምሥጢር ታላቅ ነው! ኤፌ 5፡ 32

ምስል
  “ዐቢይ ውእቱ ዝ ነገር!”/ “ይኽ ምሥጢር ታላቅ ነው!”/ “τὸ μυστήριον τοῦτο μέγα ἐστίν” ኤፌ 5፡ 32  የትኛው? ሦስት ነጥቦችን ላንሣ፦  እግዚአብሔር ፍጥረትን የወደደበት ዘለዓለማዊ ምሥጢር  ከልግስናው፣ ከደግነቱ፣ ከአፍቃሪነቱ ብዛት ህልውና ያልነበረውን ዓለም ካለመኖር ወደመኖር አመጣው፤ ፍጥረትን ኹሉ ወክሎ ሲጠራ አቤት ብሎ ለተወደደበት ፍቅር ምላሽ መስጠት የሚችል የሰውን ልጅም በፍጥረቱ ላይ ጉልላት አድርጎ አኖረ። ይኽን ያደረገበት ምክንያትም የፍጥረት ራስ የኾነው የሰው ልጅ እግዚአብሔር ፍጥረትን ለወደደበት ዘለዓለማዊ ፍቅር የፍቅር ምላሽ በመስጠት ከእርሱ ከእግዚአብሔር ጋር በፍቅር አንድ አንድ ኾኖ እንዲኖር ነው። በዚኽ አንድ በኾነበት ፍቅርም የእግዚአብሔር ብቻ የኾነው ሕያውነት ኹሉ የሰው ልጅ ሀብት ይኾናል። ክብሩን ይለብሳል። ሕይወቱን ይወርሳል። ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ስለኾነ ከዐፈር የተበጀው፣ ህልውና፣ ሕያውነት የሌለው የሰው ልጅ ሕያው፣ ህልው ይባላል። ሕያው ኾኖም ፍጥረትን ኹሉ ሕያው ያደርጋል። ራሱ ሕያው ከኾነ አካሉም ሕያው ነውና። ይኽ ከእግዚአብሔር ለፍጥረት የተለገሰ ፍቅር ፍጹም ስለኾነ ከሰው ልጅ የሚገኘው ምላሽ ምንም ቢኾን አይለወጥም። በዚኽ ዘመነ አስተርእዮ በቤተ ክርስቲያን የምናስበው፣ የምናመልከውም ይኽንን ዓለም ሳይፈጠር በፊት ጀምሮ የተወደድንበትና ዘመኑ በደረሰ ጊዜ በእግዚአብሔር ልጅ ሰው መኾን የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ዘለዓለማዊ ፍቅር ነው። ዓለም ሳይፈጠር ጀምሮ ለእኛ የነበረው እኛ የእርሱ ኾነን፣ እርሱም የእኛ ኾኖ የመኖሩን ዕቅድ ፈጸመው። ብንበድለው ይቅር ብሎ፣ ብንርቀው ቀርቦ የፍቅሩን ዕቅድ ፈጸመው። ዳግም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ነፋስ እንዳይገባ፣ መተጣጣት እ...

“አባት ልጁን ይወዳል ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል።” ዮሐ. 3፡ 37

ምስል
 የዕለቱ ግጻዌ ምንባቦች፦  ኤፌ 5፡ 21 ፤ ራእ 21፡ 1 ሐዋ 21፡ 31 መዝ 127፡ 2 ዮሐንስ 3፡ 25    “አባት ልጁን ይወዳል ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል።” ዮሐ. 3፡ 37 ዛሬ የሰማናቸው ምንባቦች በሙሉ (ከሐዋርያት ሥራ በስተቀር) “ሙሽራ” “ሙሽሪት”፣ ባል፣ ሚስት የሚል ቃል አላቸው። የዕለቱ መዝሙርም “ ትዌድሶ መርዓት ” (ሙሽሪቱ ታወድሰዋለች [ሙሽራዋን]) ይባላል። ዮሐንስ መጥምቅ “ሙሽራዪቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው” ሲል፣ ዮሐንስ ባለራእዩ “ወደዚኽ ና፣ የበጉን ሚስት ሙሽራዪቱን አሳይኻለኹ” የሚል ድምፅ ከመሪው መልአክ መስማቱን ይነግረናል። ቅዱስ ጳውሎስም “ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እንደወደዳት… ስለእርሷ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ” ሲል ሰምተነዋል። ስለዚኽ ሙሽርነት ለመነጋገር ግን መነሻው ነጥብ ከላይ የጠቀስነው እውነት ነው። “አባት ልጁን ይወዳል፤ ኹሉንም በእጁ ሰጥቶታል።” ሦስት ነጥቦችን እናንሣ፦   የሙሽርነት መጀመሪያ  እግዚአብሔር አብ ልጁን በፍጹም ፍቅር፣ በፍጹም ልግስና ይወድዳል። ስለዚኽም እርሱ በአባትነቱ፣ በእግዚአብሔርነቱ ያለውን ኹሉ አምላክነቱን፣ ብርሃንነቱን፣ ሕይወትነቱን ያለ አንዳች ንፍገት፣ በፍጹም ልግስና ሰጠው። አብ ለወልድ ያልሰጠው አንዳችም ነገር የለም፤ እውነተኛ አባት ነውና። ከልግስናው ብዛት የተነሣም በልጁ በኩል የእርሱን ሕይወት የሚወርስ ፍጥረትን መፍጠር ወደደ። ወድዶም በቃሉ ካለመኖር ወደ መኖር አመጣት፤ ከእርሱ ሕያውነት የተነሣ ከዘለዓለም ሕያው በኾነው ልጁ በኩል የእርሱን ሕይወት ወርሳ የምትኖር፣ የሰው ልጅ ራሷ፣ ጉልላቷ የኾነላት ፍጥረትን በአንድ ልጁ አበጀ። በልጁ፣ ለልጁ ስላበጃት፣ የልጁን ሕይወት ወርሳ የምትኖር ስለኾነችም የልጁ ትዳር፣ የልጁ ሙሽ...