ልጥፎች

ከጁላይ, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

“ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቷችኋል።”

፪ኛ፡ ቆሮ፡ ም. ፱፥ቍ. ፮-ፍ፡ም፤ ያዕ፡ ም. ፫፥ቍ. ፲፫-ፍ፡ም፤ ግብ፡ ሐዋ፡ ም. ፳፯፥ቍ. ፳-፳፮፤ ማቴዎስ፡ ም. ፲፫፥ ቍ. ፲፰-፳፬  ከሠኔ 25 እስከ መስከረም 25 ያለው ጊዜ ዘመነ ክረምት ይባላል። የዛሬ ምንባቦችም ክረምት፣፣ ዘር መዝራት፣ ፍሬ መስጠት የሚሉ ጭብጦችን ያነሣሉ። መዝሙረኛው እግዚአብሔርን “ለእንስሳት ሣርን የሚያበቅል፣ የሰውንም እርሻ በልምላሜና በፍሬ ባርኮ የሚመግብ እንደኾነ እያነሣ እግዚአብሔርን በመጋቢነቱ ያመሰግናል።  ቅዱስ ጳውሎስ የቆሮንቶስን ምእመናን ሀብቱን ለድኾችና ለችግረኞች የቤተ ክርስቲያን አባላት የዘራ ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ ዕጥፍ ድርብ በረከት እንደሚቀበል እየነገረ የልግስናን ገበሬዎች ያበረታታል። ቅዱስ ያዕቆብም ሰው በልቡ ውስጥ የእግዚአብሔርን ጥበብ ቢዘራ ንጽሕና፣ ዕርቅ፣ ገርነት፣ ትሕትናን፣ ምሕረትን እንደሚያበቅል ይናገራል። ሰው በልቡ ውስጥ የአጋንንትን ጥበብ ቢዘራ ደግሞ ቅንዓት፣ አድመኛነት፣ ሑከት፣ ክፉ ሥራ ሁሉ እንደሚበቅሉበት በግልጽ ያስተምራል። የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚታዩት ፍሬዎች የትኞቹ ናቸው? በአጥቢያችን የሚታዩት ፍሬዎችስ የትኞቹ ናቸው? በእኔ ሕይወት ውስጥ የሚታዩት ፍሬዎችስ? ከአንደበታችን የሚወጣው፣ ከአኗኗራችን የሚንጠባጠበው ፍሬ በልባችን ውስጥ የማንን ጥበብ ዘርተን እንደምንኖር ይመሰክርል/ብናል። የሐዋርያት ሥራ ምንባብ ደግሞ በልቡ የእግዚአብሔር ጥበብ የኾነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የዘራው ገበሬ ቅዱስ ጳውሎስ በእሥረኝነት ኾኖ አሣሪዎቹን ሲያጽናና ያሳየናል። የወንጌል ምንባባችንም ጌታ ኢየሱስ የዘሪውን ምሳሌ ለደቀ መዛሙርቱ ሲያብራራላቸው እንመለከታለን። በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ጌታ ኢየሱስ ይኽን ማብራሪያውን የሚጀምረው ግን ዛሬ ከተነበበው ክፍል ጥቂት ከፍ ብሎ ነው።...