ልጥፎች

ከማርች, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

“በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻ አወጣን።”

ምስል
ገላትያ 5፡1፤ ያዕቆብ 5፡ 14 ፤ ሐዋ 3፡ 1፤ መዝ 40፡ 3 ፤ ዮሐ. 5፡ 1  የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት ላይ ነን። መጻጕዕ ይባላል። ይኽ ሳምንት ጌታ ኢየሱስ ድውያንን መፈወሱን የምታስብበት ነው። በጾመ ድጓዋ “ብውሕ ሊተ እኅድግ ኃጢኣተ በዲበ ምድር፤ እስብክ ግዕዛነ፣ ወእክሥት አዕይንተ ዕውራን፤ አቡየ ፈነወኒ።” (በምድር ላይ ኃጢኣትን ይቅር እል ዘንድ፣ ነጻነትን እሰብክ ዘንድ፣ የዕውራኑን ዓይኖች እከፍት ዘንድ አባቴ ላከኝ) እያለች ወልድ ከአብ ዘንድ ተልኮ ነጻ ያወጣን ዘንድ እንደመጣ ትዘምራለች። በወንጌል የተጠቀሱትን የጌታ የፈወሳቸውን እየጠቃቀሰች ታዜማለች። ከደስታዋም ብዛት “በሰንበት ፈወሰ ዱያነ፤ ወከሠተ አዕይንተ ዕውራን በሰንብተ፤ ፈድፋደ ኪያነ አፍቀረነ።” (በሰንበት ሕሙማንን ፈወሰ፤ የዕውራኑን ዓይኖች ከፈተ፤ እኛን እጅግ ወደደን!) ትላለች። በዚኽ እሑድ የሚነበቡት ምንባባትም ኹሉ ስለ ሕመም፣ ስለ ፈውስ እና ስለ ነጻነት ይናገራሉ። ዋናው ጉዳይ ግን መታመም ወይም መፈወስ ሳይኾን እግዚአብሔር በአንድ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በሠራውና ዛሬም አካሉ በኾነችውና መንፈሱን በለበሰችው ቤተክርስቲያኑ በሚሠራው ሥራ ለሰው ልጅ የሰጠው ዘለዓለማዊ ግዕዛን (ነጻነት) ነው። በዚኽ አጀንዳ ላይ ሰዎች የእግዚአብሔርን ሐሳብ ምን ያኽል እንደማይረዱት በዮሐንስ ወንጌል 5 ላይ ያለው ለ38 ዓመታት ታምሞ የኖረው ሰው ታሪክ በግልጽ ያሳያል። በዚኽ ታሪክ ውስጥ ሦስት የተለያዩ አካላትን እንመለከታለን።    አንድ፦ ታማሚው ሰው  ታማሚው ሰው 38 ዓመት በሥቃይ ኖሯል። ተንገላትቷል። ፈውስ ጠብቆ አላገኘም። ሮጦ መያዝ፣ ሠርቶ መክበር፣ ሌሎች ሰዎች የሚያደርጉትን ማድረግ አልኾነለትም። ስለዚኽ፣ “ከሰዎች አንሻለኹ! ስላነስኹም እኔን የሚወድደ...